የ1 ሚሊዮን ብር የቦንድ ግዥ ተፈጸመ

ካም ሴራሚክስ ፕሮዳክት ኃላ.የተ.የግ.ማ. በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መ/ቤት በመገኘት ሚያዝያ 09 ቀን 2010 ዓ.ም. የአንድ ሚሊዮን ብር ቦንድ ገዛ፡፡

በዕለቱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ቦንድ ሰርተፊኬት ርክክብ ተደርጓል፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታሁን ናና በዕለቱ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደንበኛ ሆኖ ገና በፕሮጀክት ትግበራ ሂደት ላይ እያለ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ በገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረጉን አድንቀው ሌሎችም ተመሳሳይ ተግባር እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር በበኩላቸው የቦንድ ግዥው የተፈጸመው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበትን ሰባተኛ ዓመት አስመልክቶ ለባለሃብቶች በተደረገው ጥሪ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ኢንጂነር ማትያስ በትረ እንዲሁ ባደረጉት ንግግር ይህን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለን የድርሻችንን መወጣት በመቻላችን መታደል ነው፤ የግድቡ ግንባታ ፍጻሜውን እስኪያገኝ ድረስ ከዚህ ቀደም እንዳደረግነው ሁሉ ለወደፊቱም ድጋፋችን የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡