የባንኩ ሠራተኞች በእግር ጉዞው ላይ ተሳታፊ ሆኑ  

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሠራተኞች 156ኛውን የዓለም ቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ቀንን በማስመልከት በጎ ፈቃደኝነት ለሰብዓዊነት” መሪ ቃል ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በተዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ ላይ ተሳታፊ ሆኑ፡፡

 

 

የእግር ጉዞውን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ነው፡፡

በሁነቱ ላይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማንን ጨምሮ፣ የማኅበሩ የሥራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተሳትፈዋል፡፡

ባንኩም  ቲ-ሸርቶችን በመግዛት ሀነቱን ስፖንሰር ማድረጉ ታውቋል፡፡