ባንኩ የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ስብሰባ አካሄደ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት ስብሰባ ጥቅምት 18 እና 19 ቀን 2010 ዓ.ም. አካሄደ።
የበጀት ዓመቱ የ1ኛው ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በስትራቴጂ፣ ለውጥና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቀርቦ በከፍተኛና መካከለኛ የማኔጅመንት አባላት ዘንድ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በሁለተኛው ቀን ውሎው ደግሞ የባንኩ የብድር ፖሊሲ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሂዶ ግብዓቶች ተወስደዋል፡፡
Awareness Raising Program on Critical Mass Cyber Security
An Awareness Raising Program on Critical Mass Cyber Security Requirement was organized for top and middle level management members of the Development Bank of Ethiopia (DBE) on August 23, 2017 at the Ministry of Trade Meeting Hall.
DBE and Information Network Security Agency (INSA) organized the Program.
The main focuses of the program was to raise awareness on the overall sections of Critical Mass Cyber Security Requirement Standard.
During the session, INSA’s Deputy Director, Major Biniam Tewelde gave some general briefing about Cyber Security and the National Information Management Centre Head, Ato Temesgen Qitaw presented two topics one specific to financial institutions and the other on critical mass training.
They stressed information integrity is important for decision making and public service delivery, and adding that the main threat is lack of awareness and then incompetence. Therefore, they recommend the Bank to take immediate action to effectively implement Critical Mass Cyber Security Requirement Standards. Finally, thorough discussion was done among the participants about the alarmingly increasing threats of cyber-attacks which are causing increasing damage to companies, organizations and governments.
የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች የ2.2 ሚሊዮን ብር ቦንድ ገዙ
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሠራተኞች ነሐሴ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መ/ቤት በመገኘት የ2.2 ሚሊዮን ብር የታላቁን ህዳሴ ግድብ ቦንድ ገዙ፡፡
በባንኩ የፋይናንስና ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ እንዳልካቸው ምህረቱ በመግቢያ ንግግራቸው ሠራተኞቹ በፈቃዳቸው የታላቁን ህዳሴ ግድብ ቦንድ በመግዛት የግድቡ ግንባታ ከፍጻሜው ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ መሳተፋቸውን አመስግነው ይህ የልማት አስተዋጽኦ ለወደፊቱም ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመቀጠል የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ በበኩላቸው ይህ አስተዋጽኦ የተደረገው ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በሠራተኞቹ ዘንድ በመሠራቱ ነው ብለዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ኃይሉ አብርሃም በበኩላቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተመሳሳይ አቋም እንዲኖረው ያደረገ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው ቦንድ በመግዛት ድጋፋቸውን ያሳዩትን የድርጅቱ ሠራተኞች አመስግነዋል፡፡
ሲሳይ ተስፋዬ እርሻ ልማት
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኮርፖሬት ማስተዋወቅና ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ባልደረቦች ወደ ደቡብ ኦሞ ዞን በመጓዝ በባንኩ ፋይናንስ ከተደረጉ ፕሮጀክቶች መካከል በ2000 ዓ.ም. በ 3 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል እና ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በተገኘ የ36 ሚሊዮን ብር ብድር በሥራ ላይ ከሚገኘው የሲሳይ ተስፋዬ እርሻ ልማት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ተስፋዬ ጋር ቆይታ አድርገዋል። መልካም ንባብ።