ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ መጠን ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ባንኩ የኮር ባንኪንግ ሲስተሙን የበለጠ ለማዘመን እና ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳው ዘንድ ከህዳር 9 ቀን እስከ ህዳር 11 ባሉት ቀናት መደበኛ አገልግሎቱን የማይሰጥ መሆኑን እየገለፅን ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ገንዘብ ለማስገባት የሚፈልጉ ደንበኞች በተቻለ መጠን እስከ ህዳር 9 ቀን 2013 ገቢ ክፍያዎችን እንዲፈፅሙ እያሳሰብን ከህዳር 10 እስከ ህዳር 12 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ገቢ ክፍያዎችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ እና ወጋገን ባንክ ቅርንጫፎች መፈፀም እንደምትችሉ ለክቡራን ደንበኞቻችን በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

                  የኢትየጵያ ልማት ባንክ፤ የልማት አጋርዎ!