የባንኩ ሰራተኞች “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርኃ ግብር ላይ ተሳተፉ

በሀገር አቀፍ ደረጃ ህዳር 08 ቀን 2013 ዓ.ም፣ ከረፋዱ 5፡30 ላይ “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ!” በሚል መሪ ቃል በተከበረው ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰራተኞች ተሳተፉ፡፡ 

ለመከላከያ ሰራዊታችን ያለንን ክብር በመግለፅ ከጎኑ መቆማችንን ለማረጋገጥ በተዘጋጀው በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው /ፒ.ኤች.ዲ/፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የሥራ መሪዎችና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡