ባንኩ በአውደ ርዕይ እና ባዛር ላይ እየተሳተፈ ነው

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከታህሳስ 21 እስከ 27 ቀን 2013 ዓ.ም በሚቆየው ሀገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይና ባዛር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

 

አውደ ርዕዩ “ሀገራዊ ጥሪ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት’’ በሚል መሪ ቃል ሜክሲኮ በፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለሥልጣን ቅጥር ጊቢ ውስጥ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ ተከፍቷል፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተ/ም/ፕሬዚዳንት-አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግን አቶ ይልማ አበበን ጨምሮ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የአውደ ርዕዩ አዘጋጅ ባለስልጣን መ/ቤት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዚህ አውደ ርዕይና ባዛር ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ምርትና አገልግሎቱን በማስተዋወቅ እና ቦንድ በመሸጥ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡