ባንኩ በተለያዩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ዙሪያ ወርክሾፕ አካሄደ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከታህሳስ 09 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ቢሾፍቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስትቲዩት በባንኩ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ወርክሾፕ አካሄደ፡፡

 

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው /ፒ.ኤች.ዲ/ አወያይነት ለ6 ቀናት በተካሄደው ዎርክሾፕ ላይ የባንኩ ም/ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የስራ መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ወርክሾፑ ላይ ውይይት ከተደረገባቸው ዋና ዋና ፖሊሲዎችና መመሪያዎች መካከል የባንኩ የብድር ፖሊሲና ፕሮሲጀር፣ የሊዝ ፋይናንሲንግ ፖሊሲና ፕሮሲጀር፣ የሰው ኃብት ፖሊሲ፣ የአይ.ሲ.ቲ ፖሊሲ፣ የግዥ ፕሮሲጀር፣ ራይት ኦፍ/ራይት ባክ /write-off/write-back/ ፖሊሲ፣ የዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ፖሊሲ፣ የትሬዠሪና ፈንድ ማኔጅመንት ፖሊሲ እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ዲስክሎዠር ፖሊሲ ናቸው፡፡

በዚህ የቡድን ስራና ውይይት ላይ ባንኩ ለጀመረው የለውጥ እርምጃ ግብዓት መሆን የሚችሉ እና በባንኩ ውስጥ ሊሰሩ ለታቀዱ የለውጥ  ስራዎች ግብዓት የሚሆኑ እንዲሁም ባንኩን የሚያዘምኑ በርካታ ሃሳቦች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በወርክሾፑ መዝጊያ ላይ የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮርፖሬት አገልግሎት አቶ ሰፊዓለም ሊበን ባደረጉት ንግግር ይህ በፖሊሲና ፕሮሲጀር ስራዎች ላይ መሰረት ያደረገው ወርክሾፕ እንዲሁም የቡድን ውይይት የባንኩን አሰራር ከማዘመን አልፎ ግልጽና አሳታፊ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት በየቡድኖቹ ለነበረው ትጋትና ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበው በዚህ የተነሳሽነት ስሜት የወርክሾፑን ግብዓቶች ወደተግባር መለወጥ ከተቻለ ባንኩን ወደተሻለ ከፍታ የማድረስ አቅም ያለው በመሆኑ ሁሉም የባንኩ አመራርና ሰራተኛ ለተጀመረው ስራ የበኩሉን አስተዋጽዖ እንዲያደርግ መልእክት አስተላፈዋል፡፡