ባንኩ ለመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር 15 ሚሊዮን ብር

 ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር  አባላትና ሰራተኞች በሜቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር  እሁድ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት የአስራ አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ የማድረግና ከ4000 በላይ ለሆኑ አረጋውያን የምሳ ማብላት መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ በመገኘት የአስራ አምስት ሚሊየን ብር ቼክ ያበረከቱት የባንኩ ፕሬዝዳንት ዮሐንስ አያሌው /ፒ/ኤች.ዲ/ ሲሆኑ ባደረጉት ንግግርም የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር እያከናወነ ያለውን በጎ ተግባር አድንቀው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለመቄዶኒያ የሚያደርገው ድጋፍ በዚህ ብቻ የሚቆም ሳይሆን ለወደፊትም አቅሙ በፈቀደው መጠን ከማህበሩ ጎን እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡

የመቄዶኒያ በጎ አድራጎት ማህበር መስራችና ባለቤት የክብር ዶክተር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ማህበሩ በተቸገረበት በዚህ ፈታኝ ሰዓት ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያደረገው ድጋፍ እጅግ እንዳስደሰታቸው በመግለፅ በማህበሩ እና በተረጂ ወገኖች ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡