የኢትዮጵያ ልማት ባንክ  ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሲሰጥ የቆየው ሃገር አቀፍ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዘጋጅነት ከመጋቢት 13 - 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ በአበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች/ማዕከላት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና አርብ የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡

 

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ሰልጣኞች እንደተናገሩት ስልጠናው በጣም ጠቃሚ ነጥቦች የተነሱበት እየሰሩት ላለውም ሆነ ሊሰሩ ላሰቡት ስራ መሰረታዊ የሆነ ግንዛቤ የያዙበት በመሆኑ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ባንኩም ይህን ስልጠና ስላዘጋጀ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡

ለወደፈቱም ባንኩ ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት የሊዝ ፋይናንሲንግ ተበዳሪዎች አቅም የማጎልበት ስራ መስራት፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ቢቀጥል እንደባንክም ሆነ እንደ ሃገር ውጤታማ ስራ መስራት ያስችለዋል ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡  

ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአምስት የስልጠና ማዕከላት ማለትም በአዲስ አበባ፣ በባህር ዳር፣ በጅማ፣ ደሴና ጅግጅጋ ሲሰጥ በቆየው ስልጠና ላይ 1500 የሚሆኑ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡