የባንኩ ሰራተኞች ድምጻቸውን አሰሙ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰራተኞች “ብሔራዊ ክብር በሕብር” በሚል በሀገራችን ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ዓይነት የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00-11፡00 በዋናው መ/ቤት ፊት ለፊት በመገኘት ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ 

በእለቱም፡-

  1. "የውጭ ኃይሎች እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ እንድታነሱ እንጠይቃለን!"
  2. "ግድቡ የእኔ ነው!"
  3. :በሀገራችን ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ዓይነት ጣልቃ ገብነትና ጫናን አንቀበልም!"
  4. "በሀገራችን የተጀመረውን ልማት እንደግፋለን!”

የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡