ታላቅ የምስራች በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ስራ  ላይ ለተሰማራችሁ እና ለወደፊቱ እቅዱ ላላችሁ የቀረበ የሥልጠና ማስታወቂያ ጥሪ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫ መሠረት በማድረግ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ፣ በማዕድን ልማት፣ በቱሪዝም ኢንዱስትሪ፣ በእርሻ እና በአግሪካልቸራል መካናይዜሽን አገልግሎት የሥራ ዘርፎች ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት /የማምረቻ መሣሪያ አቅርቦት በስፋት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ባንኩ አሰራሩን በአዲስ መልክ በማዘመን እና ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሀገሪቱ ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለምታደርገው መዋቅራዊ ሽግግር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ኢንተርፕራይዞች የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እና የሚሰሩትን ሥራ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ለማድረግ ባንኩ በቢዝነስ ፕላን ዝግጅት እና ርዕይ ቀረጻ፣ የፋይናንሽያል ዝግጅትና ትንተና፣ የቢዝነስ አስተዳደር፣ የሰው ኃብት አመራር፣ የገበያ ጥናት፣ የፖሊሲ ቅኝት እንዲሁም የሊዝ ፋይናንሲንግ አሰራር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ከዚህ ቀደም በስምንት ማዕከላት ማለትም በአዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ጂግጂጋ፣ ደሴ፣ ጂማ፣ አዳማ፣ ወላይታ ሶዶ እና ቡታጅራ ከተሞች ላይ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ አሁንም ይህንኑ በማስቀጠል በትግራይ መቀሌ ማእከል ስልጠናውን ለመስጠት ባንኩ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ሥልጠናውን እንዲወስዱ የታሰቡ ተሳታፊዎች 1ኛ) ከባንኩ የፕሮጀክትና የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት እያገኙ ያሉና በሥራ ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች 2ኛ) ለመሳተፍ ቢዝነስ ፕላን ለባንኩ ያቀረቡ ወይም ለማቅረብ የተዘጋጁ 3ኛ) እውቀቱ፣ ሙያው እና አቅሙ ያላቸው ቢዝነስ ፕላን ለማዘጋጀት የሚፈልጉ እና ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልተው የባንኩን ድጋፍ የሚፈልጉ አዲስ ኢንተርፕራይዞችንም ጭምር ይመለከታል፡፡

የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ከባንኩ ለማግኘት በቅድሚያ ባንኩ ያዘጋጀውን ይህንን ሥልጠና መውሰድ ባንኩ ለሚሰጠው አገልግሎት እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚወሰድ መሆኑ ታውቆ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቀሌ ዲስትሪክት  ጽ/ቤት እና በስሩ በሚገኙ ቅርንጫፎች በመገኘት እንድትመዘገቡ እና ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ሥልጠናውን በአግባቡ እንድትከታተሉ ባንኩ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

ሥልጠናው የሚመለከተው የድርጅቱ ባለቤት ወይም ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይም ከድርጅቱ የውክልና ደብዳቤ የሚያቀርብ ሲሆን ሃሳብ እና ፍላጎቱ ብቻ ያላቸው ማሳሰቢያው አይመለከታቸውም፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የልማት አጋርዎ!!