ስለ ኖቭል ኮሮና ቫይረስ /COVID 19/ ማወቅ የሚገባዎ ጥቂት ነጥቦች

 

በቻይናዋ ዉሃን ግዛት የተከሰው ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጪ አገራችንን ጨምሮ ወደ በርካታ አገራት እየተዛመተ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ለግንዛቤዎ ይረዳዎ ዘንድ ስለ ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ምንነት እና እንዴት  መጠንቀቅ እንደሚገባ የሚከተሉትን ሀሳቦች አስፍረናል፡፡

ኮሮና ቫይረስ ምንድነው?

የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው።

የቫይረሱ መተላለፊያ መንገዶች

በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ።

የበሽታው ምልክቶች

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል።

በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ የሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋላል።

በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ምልክቶች

  • ቫይረሱ መጀመሪያ ጉሮሮን ያጠቃል፤ ስለዚህ ለ3 ወይም 4 ቀናት የሚቆይ የጎሮሮ ህመም ይኖራል፡፡
  • ከፍተኛ ትኩሳት ያመጣል፡፡
  • ከዚያም ቫይረሱ ከአፍንጫ ፈሳሽ ጋር ይዋሃድና አየርን ከአፍንጫ /ከአፍ/ ወደ ሳንባ የሚያመላልሰውን ቱቦ /trachea/ ያጠቃል፡፡ በመቀጠል ሳንባ ውስጥ ይገባና የሳንባ ምች /pneumonia/ ያስከትላል፡፡ ይህ ሂደት 5 ወይም 6 ቀናት ይወስዳል፡፡
  • የሳንባ ምች ከፍተኛ ትኩሳት እና የመተንፈስ ችግር ያስከትላል፡፡
  • በቫይረሱ ምክንያት የሚመጣውን የአፍንጫ መታፈን በጉንፋን ምክንያት ከሚያጋጥመው የተለመደ ዓይነት መታፈን ጋር ተመሳሳይ አይደለም፡፡ የመዘጋት፣ አየር የማጠር እና ራስን መቆጣጠር ያልቻሉ እንደሆነ ይሰማዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ አፋጣኝ ትኩረት እና ክትትል ያስፈልግዎታል፡፡
  • በበሽታው መያዝዎን ወይም ምልክቱ የታየባቸውን ሰዎች ሲያጋጥምዎ ሪፖርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመር 8335 ወይም የመደበኛ ስልክ 0112-765340 መጠቀም ይችላሉ።

 

ስለ ቫይረሱ ተጨማሪ መረጃዎች

ይህ አዲስ በሽታ አምጪ ቫይረስ የጸሐይ ብርሃንን ጨምሮ ሙቀትን መቋቋም የሚችል አይደለም፤ በ26/27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በሆነ የሙቀት መጠን የሚሞት ነው፡፡

በቫይረሱ የተጠቃ አንድ ሰው ቢያስነጥስ፤ ቫይረሱ መሬት ሳያርፍ በአየር ላይ መንሳፈፍ እና መጓዝ የሚችለው ለ10 ጫማ ያህል ነው፡፡

ቫይረሱ በብረት ነገሮች ላይ ቢያንስ ለ12 ሰዓታት ያህል በህይወት መቆየት የሚችል ሲሆን ስርጭቱን ለመከላከል እና በቫይረሱ እንዳይጠቁ ማንኛውንም ብረት ነክ እቃ በነኩ ቁጥር ወዲያውኑ እጅን በንጽህና መጠበቂያ ኬሚካል (ሳሙና) በደንብ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ በጨርቅ ነክ (fabric) ላይ ከ6-12 ሰዓታት በህይወት ሊቆይ ይችላል ሆኖም የተለመደው የልብስ ማጠቢያ ሳሙና ይገድለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የሞቀ ውሃ መጠጣት ሁሉንም የቫይረስ ዓይነቶች ለማዳከም ውጤታማ ነው፡፡ ስለሆነም ፈሳሾችን ከበረዶ ጋር ሳይቀላቅሉ በብዛት መጠጣት ይመከራል፡፡

ኮሮና ቫይረስ በእጅ ላይ ከ5-10 ደቂቃ ብቻ በህይወት ሊቆይ ይችላል፡፡ ስለዚህ እጅን ደጋግሞ በሳሙና ማጠብ ያስፈልጋል፡፡ ከታጠቡ በኋላም ቢሆን እጅ ላይ ቫይረሱ ሊኖር ስለሚችል ዓይንን እና አፍንጫን መነካካት አያስፈልግም፡፡ ሞቅ ባለ ውሃ ትንሽ ጨው በመጨመር አፍን መጉመጥመጥ እና ከኢንፌክሽን ነጻ ማድረግ ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር ንክኪ ማቆም ለምሳሌ አለመጨባበጥ፣ ሰዎች በብዛት በሚሰበሰቡበት እና መጨናነቅ ባለበት ቦታ አለመገኘት ይመከራል፡፡ 

በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ምን ማድረግ አለባቸው?

ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካለብዎ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ።

የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረም ይህንንም ለጤና ባለሙያ ያሳውቁ።

በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ።

አፍን አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።

በሽታው ወዳለባቸው ሃገራት ሲጓዙ ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች

ትኩሳት እና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ፣ ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋጽዖዎችን አለመመገብ፣ በሕይወት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤት እና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ፣ በተጨማሪም ስለ በሽታው በቂ መረጃ እንዲኖረዎ የሚመለከታቸውን አካላት ይጠይቁ፡፡

ተጨማሪ

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ በመጀመሪያ አንድ ጃፓናዊ አሁን ደግሞ 3 ጠጨማሪ ግለሰቦች /3 ጃፓኖችና 1 ኢትዮጵያዊ/ መያዛቸውንና እነርሱንም አስቀድሞ በተዘጋጀው የለይቶ ማከሚያ ተገቢው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ፣ እንዲሁም ከበሽተኞቹ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችም እንዲሁ ተለይተው አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የጤና ተቋማቱ መንግሥት የበሽታውን ሥርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ተገቢውን እርምጃ እየወሰደ መሆኑን እንደሚያረጋግጡ በመግለጽ፣ ማኅበረሰቡ የመከላከያ መንገዶችን ችላ ሳይልና ሳይደናገጥ ተግባር ላይ በማዋል የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፡- ሪፖርትር ጋዜጣ፣ ፋና፣ ቢቢሲ አማርኛ እና ሌሎችም