Development Bank of Ethiopia
Toggle Navigation
  • Home
  • Contact Us
  • About
    • Mission, Vision and Value
    • History
    • Bank Mandates
    • Board Memebers
    • Excutive Members
    • Organizational Stracture
  • Services
    • Banking Services
    • Bond Issuing
    • Loan Requirments
    • Rural Electrification
    • Priority Sectors
    • Export Credit Gurantee
    • International Banking
    • Project Financing
    • RUFIP
  • Publication
    • Annual Report
      • 2021
      • 2020
      • 2019
      • 2018
      • 2017
      • 2016
      • 2015
      • 2014
      • 2013
    • Brochure
    • Zena Lemat Bank
    • Bond Flayer
    • Dev't News Letter
      • News Letter 1
      • News Letter 2
      • News Letter 3
      • News Letter 4
      • News Letter 5
  • Notice
    • Bid
    • Foreclosure
    • Vacancy
    • Rate
  • Address
    • Head Office
    • Directorate/Office
    • Districts and Branch Offices
  • FAQ
  • banner1.jpg
  • banner3.jpg
  • banner4.jpg
  • Development-partner2.jpg
  • Mining.jpg
Previous Next Play Pause
  • Credit ServiceCredit Service
  • RUFIPRUFIP
  • BondBond
  • IBSIBS
  • ECGECG

 

በሥልጠና ለተሳተፉ አስተባባሪዎች የምስጋና መርሐ ግብር ተካሔደ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሦስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሥልጠና በአስተባባሪነት የተሳተፉ ሠራተኞቹን ያመሰገነበትን መርሐ ግብር አርብ፣ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በባንኩ ስብሰባ አዳራሽ አካሒዷል፡፡

ከግንቦት 5 እስከ ግንቦት 27 ቀን 2014 ድረስ ባሉ ቀናት በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተካሔደውን ሥልጠና በዐቢይና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተደራጅተው ላስተባበሩ የባንኩ ሠራተኞችና ሥራ ኃላፊዎች የባንኩ ፕሬዚዳንት ክቡር ዮሐንስ አያሌው/ፒኤ.ች.ዲ/ በተገኙበት የምስጋናና እውቅና መርሐ ግብሩ ተካሂዷል፡፡ 

የባንኩ ፕሬዚዳንት በመድረኩ ተገኝተው ለአስተባባሪዎች የምስክር ወረቀት በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት በዐቢይ ኮሚቴው ጥብቅ ክትትል በየማእከላቱ በሚገኙት ኮሚቴዎች መነቃቃትና ትጋት በሚፈለገው ደረጃ ሥልጠናው መመራቱ ስኬታማና ውጤታማ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል፡፡ ለዚህም በሁሉም ደረጃ ለነበሩ አስተባባሪዎች እና ሠራተኞች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት አክለው በዚህ ደረጃ ያለን ግዙፍ ሀገር አቀፍ ሥልጠና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ባንኩ ልምድ ሊቀሰምበት የሚገባ ታሪካዊ አፈጻጸም አስመዝግቧል ብለዋል፡፡ በ20 ከተሞች በተካሔደው በዚህ ሥልጠና ከ27 ሺህ በላይ ሠልጣኞች መሳተፋቸው ይታወሳል፡፡

                                         

                               የባንኩ የሕንፃ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአዳማ ዲስትሪክት ሊያስገነባው ላቀደው ሁለገብ ሕንጻ የተዘጋጀው የመሠረት ድንጋይ የባንኩ ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎችና አዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በተገኙበት ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ተቀመጠ፡፡

በ208 ሚሊዮን ብር ወጪ እንዲሠራ የታቀደለት ይኸው ሕንፃ ባለ ስምንት ወለል ሕንፃ ሆኖ ምድር ቤትና ግራውንድ የሚኖረው ሲሆን፣ የባንኩ የአዳማ ዲስትሪክት ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማቀላጠፍ አንደሚያስችል የታመነበት ነው፡፡

የመሠረት ድንጋዩ በተጣለበት በዚህ ሥነ ሥርዓት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሰፊ ዓለም ሊበን በንግግራቸው እንዳመለከቱት   ባንኩ ደንበኞችን ለማገልገል ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎትን ከማምጣት ባሻገር የሠራተኞች ካፍቴሪያና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ /gymnasium/፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ወዘተ የሚኖሩት ሲሆን፣ ከባንኩ አሠራር ጋር በማይጋጭ መንገድ ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ የሚከራዩ ሱቆችንም እንዲይዝ ተደርጎ የሚገነባ ይሆናል። የሕንፃ ግንባታው ከሁለት እስከ ሦስት ዓመታት ብቻ ሊወስድ አንደሚችል የጠቆሙት አቶ ሰፊዓለም የሕንጻው ዲዛይንም ባንኩ በሌሎች ክልሎች ለሚያስገነባቸው መሰል ሕንፃዎች እንደ ሞዴል ሊወሰድ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የከተማው ክንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ በበኩላቸው የአዳማ ከተማን ‹‹ስማርት›› ከተማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ልማት ባንክ ስሙን የሚመጥን እና ለልማት ያለውን አጋርነት በሚያሳይ መንገድ ይህን ሁለገብ ሕንፃ ለመሥራት መነሣቱን እናደንቃለን ብለዋል፡፡ ልማት ባንክ ለሚያከናውናቸው ተግባራትም የከተማ አስተዳደሩ ከጎኑ መቆሙን አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አዳማን ጨምሮ ዋና ዋና ከተሞች በሚገኝ 12 ዲስትሪክቶችና 78 ቅርንጫፎች እንዳሉት ይታወቃል፡፡

 

 

በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገ ሥልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሳይበር ድህንነትን ማእከል ያደረገ ሥልጠና ለሠራተኞቹ ሰጠ፡፡

በግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም በባንኩ የስብስባ አዳራሽ ባዘጋጀው ሥልጠና በዓለም ከፍተኛ ስጋት ሆኖ የመጣውን የሳይበር ጥቃትና ደኅንነት በማስመልከት የግማሽ ቀን ሥልጠና ለ34 ሠራተኞቹ የሰጠ ሲሆን፣ ሥልጠናውን ያዘጋጁት የባንኩ የአይቲ እና ሰው ኃይል ዳይሬክቶሬቶች በጋራ ነው፡፡ ሥልጠናው በዓመቱ ለአራት ጊዜያት የሚካሔድ ሆኖ ከሁሉም ዳሬክቶሬቶች የተውጣጡ ሠልጣኞች የሚሳተፉበት ነው፡፡

ሥልጠናውን የሰጡት የባንኩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ደኅንነት የሥራ ክፍል ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ወልደ ገብርኤል እንደገለጹት በዓለም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለው የሳይበር ጥቃት ለሀገራችንም ከፍተኛ ስጋት ሆኖ እንዳለ አመልክተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ገለጻ የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በመሰሉ የፋይናንስ ተቋማት ደግሞ በተለየ ሁኔታ ተጠቂ የሚሆኑበት ደረጃ ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ የባንኩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በዚህ ረገድ ያለውን ስጋት ለመቅረፍ ከሚወስዳቸው እርምጃዎች አንዱ ሠራተኞችን የነቁና የበቁ ሆነው እንዲሠሩ ማድረግ መሆኑን ጨምረው የገለጹት አቶ ቴዎድሮስ ለዚህ የሚያገለግሉ ቴክኖሎጂዎችን ሥራ ላይ ማዋልና የዳይሬክቶሬቱን ሠራተኞችን አቅም መገንባት በሌላ አማራጭ የተያዙ አካሔዶች ናቸው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር  በትብብር ለመሥራት የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

 

Bid Announcement (የጨረታ ማስታወቂያ)

 

Please get the bid details from the following link. (የጨረታውን ዝርዝር ለመመልከት የሚቀጥለውን ሊንክ ይጫኑ)

Bid Announcement

ባንኩ ሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አለምገነት ንግድና ኢነዱስትሪ ኃ-የተ-የግ-ማህበር

 

 

  1. ማስታወቂያ ለሥልጠና ተመዝጋቢዎች በሙሉ
  2. DBE Takes Part in Agricultural Mechanization Leasing Forum

Page 4 of 26

  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • ...
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10

Lease Finance

  • Brochure
  • Requirements
  • Feasibility study contents above 10 million
  • Business plan content below 10 million

Credit Service

  • Guide to Access DBE's Loans
  • Loan Requirments and their purpose
  • Priority Areas
  • Revised Credit Policy Feb 2018

External Fund and Credit Management Directorate

  • Press Release on Disbursement of Interest Rate Subsidy
  • Social Assessment For The Women Entrepreneurship Development Project Additional Financing (WEDP AF)
  • Environmental And Social Management Framework (ESMF) Update - Women Entrepreneurship Development Project Additional Financing
  • ESMF Final RUFIP III
  • SME Audit Report 2019/20
  • WEDP-Financial statement 2019/20
  • DBE-ENREP-Audit 2019-20.pdf
  • SME Audited Financial Statement 2018/19
  • MDRE & EEP Audited Financial Statement 2018/19
  • WEDP Audited Financial Statement 2018/19
  • ELECTRICITY NETWORK REINFORCEMENT PROJECT audit report for june 30 2018
  • WEDP (Field visit annex Audit report)
  • Audit Report Financial Statement 2018
  • Auditors' Report on WEDEP Grant
  • RUFIP News II
  • RUFIP News Updates
  • Documents
  • Electricity Network Reinforcement
  • Independent Auditor's Report
  • Audit Report 2018
  • DBE-WEDP Audit Report 2021
  • DBE-SMEFP Audit Report 2021
  • DBE-ENREP Audit Report 2021/22

DBE advert

  • DBE advertDBE advert

DBE Location

  • DBE LocationDBE Location

Branch Location

  • Branch LocationBranch Location
feed-image My Blog

Back to Top

© 2023 Development Bank of Ethiopia