የጨረታ ማስታወቂያ
መስከረም 10, 2015
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 20 ሚሊዮን ብር ለበጎ አድራጎት ስራ ድጋፍ አደረገ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እንዲሁም ለዲቦራህ ፋውንዴሽን ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም የ20 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡
ባንኩ በመንግስት ትኩረት ለተሰጡ የልማት ፕሮጀክቶች ብድር ከመስጠት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ይበልጥ ለመወጣት ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 15 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም ለዲቦራ ፋውንዴሽን ደግሞ የ5 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጀርመን ልማት ባንክ ቀጣናዊ ዳይሬክተር በሐዋሳ የሥራ ጉብኝት አደረጉ
የጀርመን ልማት ባንክ (KFW) የምሥራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ኅብረት ቀጣናዊ ዳይሬክተር ሚስተር ክሪስቶፍ ቲከንስ ሰኔ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት በመገኘት የሥራ ጉብኝት አደረጉ፡፡
ሚስተር ክሪስቶፍ ከሌሎች የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ጋር ሐዋሳ በሚገኘው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲስትሪክት በደረሱበት ጊዜ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ፒ.ኤች.ዲ) እና ሌሎች ከዋናው መሥሪያ ቤትና ከዲስትሪክቱ የተገኙ የማኔጅመንት አባላት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ሚስተር ክሪስቶፍ ቲክንስ በሥራ ጉብኝታቸው የሐዋሳ ዲስትሪክት እና ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች የሥራ ሁኔታ የጎበኙ ሲሆን፣ በዕለቱ በጀርመን ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ተገዝተው ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደንበኞች ሊተላለፉ የተዘጋጁ የኮምባይነር ሃርቨስተር ቁልፍ ለደንበኞች የመስጠት ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
Page 5 of 28