በጉለሌ ክ/ከ በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እና ወረዳ 8 በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ እንደ አዲስ ፈርሰው የተገነቡ 3 የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለነዋሪዎቹ ተላልፈዋል፡፡
በተዘጋጀው የቤት ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የባንኩ ፕሬዚዳትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማውና ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
Read more: በጉለሌ ክ/ከ በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ
በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፈርሰው እንደ አዲስ የተገነቡ 5 የአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች፣ 4 መጸዳጃ ቤቶች እና 1 ምግብ ማብሰያ ቤት ጥር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ተመርቀው የቁልፍ ርክክብ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ ፕሬዚዳትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና የወረዳ 5 ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ተገኝተዋል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ፒ.ኤች.ዲ) በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ይህ ተግባር ባንኩ በማኅበራዊ ኃላፊነት ከሚያደርጋቸው መጠነ ሰፊ ድጋፎች መካከል አንዱ ሲሆን ባንኩ ከተቋቋመበት 1901 ዓ.ም ጀምሮ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በልዩ ልዩ መንገዶች ሲወጣ የኖረ የሀገር ሀብትና ኩራት የሆነ አንጋፋ ባንክ ነው ብለዋል፡፡
በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የተሰራው “ኂሩት አባቷ ማነው?” ፊልም ተመረቀ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተሰራው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ባለጥቁርና ነጭ ቀለም “ኂሩት አባቷ ማነው?” ፊልም ዲጂታላይዝ በመደረጉ ሐሙስ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ተመርቋል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ አርቲስቶች እና በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አበቤ ፕሮግራሙን አስመልክቶ መልእክት በማስተላለፍ ፊልሙን መርቀው የከፈቱ ሲሆን በንግግራቸውም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በሆነው ታሪካዊ ፊልም ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለዚህ ታሪካዊ ፊልም ከመነሻው ጀምሮ እስካሁን ድረስ ላበረከተው አስተዋጽዖ አመስግነው፣ ፊልሙ በተለይ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው በመጡበት ሰዓት መመረቁ ሀገራችን ከጥንት ጀምሮ በኪነጥበቡ ዘርፍ አሻራዋን ስታሳርፍ ማለፏን ከመገንዘብ ባለፈ ስለ ቀደምት የኪነ ጥበብ ስራዎች መረጃ ለማግኘትና ለቀጣይ በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ለሚደረጉ ጥናታዊ ጽሑፎች መነሻ ግብዓትም ይሆናቸዋል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው በ1957 ዓ.ም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተሰራው ይህ ታሪካዊ ፊልም በወቅቱ ፊልሙ ከባንኩ በተገኘ ብድር የሰራው የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር እዳው ተሰርዞለት ፊልሙ በስጦታ እስከተበረከተበት እለት ለ40 ዓመታት ሳይበላሽ በጥንቃቄ በማስቀመጡ ባንኩን እጅግ ያስመሰግነዋል ብለዋል፡፡
አያይዘውም በ2012 ዓ.ም ዲጂታይዝድ ተደርጎ በአሁን ሰዓት በድጋሚ ለእይታ እንዲበቃ ባንኩ ላደረገው ከፍተኛ ድጋፍ በኪነጥበብ ባለሙያዎችና በዘርፉ ሥም አመስግነው ወደፊትም ባንኩ ለዘርፉ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ባንኩ በኢትዮጵያ የፊልም ታሪክ ግንባር ቀደም ሆኖ ፋይናንስ በማድረግ ላበረከተው አስተዋጽዖ የምሥጋና ምሥክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
በባንኩና ኢቢሲ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) መካከል በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ አብሮ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ታህሳስ 04 ቀን 2014 ዓ.ም በራዲሰን ብሉ ሆቴል ተፈርሟል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት ክቡር ዮሐንስ አያሌው (ፒ.ኤች.ዲ) እና የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ፍስሃ ይታገሱ የመግባቢያ ስምምነቱን ፈርመዋል፡፡
በመግባቢያ ስምምነቱ መሠረት ኢቢሲ ባንኩ ለሚሰራቸው ሚዲያ ነክ ሥራዎች፣ ልዩ ልዩ መግለጫዎች እና ማስታወቂያዎች በጣቢያው /የራዲዮና የቴሌቪዥን ሚዲየሞች/ ቅድሚያ በመስጠት የዜና ሽፋን የሚሰጥ ሲሆን ባንኩም የተለያዩ ሁነቶች ሲኖሩት ለኢቢሲ ቅድሚያ በመስጠት ሽፋን እንዲያገኝ ያደርጋል፡፡
የሁለቱም ተቋማት መሪዎች ስለ ተቋሞቻቸው አጠር ያለ ጽሑፎችን አቅርበዋል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ፒ.ኤች.ዲ) ባቀረቡት ጽሑፍ ልማት ባንክ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ነድፎ ወደ ሥራ ከገባበት በተለይም ከአንድ ዓመት ወዲህ ውጤታማ ባንክ ሆኗል፡፡ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለ ትርፍም አስመዝግቧል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም ካለፈው ዓመት የተሻለ ውጤት ለማምጣት ተግቶ እየሰራ ይገኛል፤ ምንም እንኳ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እየተካሄደ ካለው የሠላም ማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ጋር በተያያዘ ተግዳሮቶች ቢኖሩብንም ብለዋል፡፡
የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍስሃ ይታገሱ በበኩላቸው የሚዲያ ተቋሙ በሀገር ግንባታ፣ በሀገራዊ መግባባት እና ዴሞክራታይዜሽን ሂደት ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራቱን ገልጸው፤ ሁለቱም አንጋፋ ተቋማት በሀገር ግንባታ ሂደት ላይ የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከተመሠረተ ከ113 ዓመት በላይ፣ እንዲሁ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ደግሞ ከ87 ዓመት በላይ እድሜ ያስቆጠሩ አንጋፋ ተቋማት መሆናቸው ይታወቃል፡፡
Page 7 of 26