ሕጻናት ለልደታቸው በተቀመጠው ብር የቦንድ ግዥ ፈጸሙ

የአቶ በኃይሉ ዳንኤል ሶስት ህጻናት ልጆች እና ባለቤታቸው ልደታቸውን ለማክበር  የተቀመጠላቸውን ብር ለቦንድ ግዥ አውለዋል፡፡ ግዥውን የፈጸሙት ሐምሌ 08 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መ/ቤት በመገኘት ነው፡፡

በእለቱ የባንኩ ተ/ም/ፕሬዚዳንት ኮርፖሬት አገልግሎት አቶ ደሳለኝ ቦጋለ ይህ ተግባር ለሌሎች መሰል የነገ አገር ተረካቢ ህጻናት እና መላው ህብረተሰብ አርአያ የሚሆን ስለሆነ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል በማለት አበረታተዋል፡፡

በመቀጠል ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሐም በበኩላቸው መንግስት ህብረተሰቡን በማስተባበር ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ግንባታውን እየፈጸመና የውሃ ሙሌቱንም እንደጀመረ ተናግረው ሌሎችም ይህን አርአያነት ያለው ተግባር በመከተል ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ እንዲገዙ እና ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሕጻናቱ አባት ሶስቱ ልጆቻቸው እና ባለቤታቸው ልደታቸውን ለማክበር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ብር አምስት ሺህ በድምሩ የብር 20 ሺህ ብር ቦንድ በራሳቸው ተነሳሽነት ገዝተዋል በማለት ገልጸዋል፡፡