ከ 10 ሚሊዮን ብር በላይ የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት ለሚጠይቁ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች  የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ይዘት፤

የፕሮጀክቱ የአዋጭነት ጥናት ፈቃድ ባላቸው አማካሪ ድርጅቶች የተዘጋጀ መሆን ያለበት ሲሆን የጥናቱ ዋና ይዘት ቢያንስ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፡-

 1. ማጠቃለያ(Excutive summary )፡- ከስር የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ነጥቦች በአጭሩ በመዳሰስ የተጠየቀውን የሊዝ መጠን አስፈላጊነት ያረጋግጣል፡፡
 2. የፕሮጀክቱ ዳራ( Project Background)

2.1.  የአመልካቹ እና ፕሮጀክቱ መግለጫ፡- ሥም፣ አድራሻ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ የፕሮጀክቱ ዓይነት/የኢኮኖሚ ዘርፍ፣ ህጋዊ አደረጃጀት፣ ወዘተ…

2.2.  የፕሮጀክቱ/አመልካቹ አጭር ታሪክ

2.3.  የፕሮጀክቱ የንግድ ዓላማ

2.4.  የፕሮጀክቱ የቀድሞ እንቅስቃሴ (ለነባር)

2.5.  የአመልካቹ የብድር ታሪክና ያለበት ሁኔታ

2.6.  የተጠየቀው የሊዝ ፋይናንስ ዓላማና መጠን

 1. የገበያ ጥናት (Market Analysis)

በወቅቱ ድርጅቱ ሊሸጥ ያቀደውን ምርት/አገልግሎት በመግዛት ላይ ስለሚገኘው ገበያ መረጃ በማሰባሰብ በሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች  ትንተና ማድረግ፤

3.1.  ድርጅቱ የሚገኝበት ኢንዱስትሪ  የገበያው አጠቃላይ ትንተና

3.2.  ውድድር:- ተመሳሳይ ምርት ከሚያመርቱ ድርጅቶች ልቆ መታየትና የተሻለ ምርት በማቅረብ በገበያው ለይ ያለውን ቀጣይነት ማረጋገጥ

3.3.  የፍላጎት ትንተና ትንበያ (Demand Analysis)፡- የሚመረተው ምርት /አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ያገናዘበ መሆን አለበት፤ ለምሳሌ ደንበኞች ምን እንደሚፈልጉ፣ የሚመረተው ምርት ተቀባይነት፣ የህብረተሰቡን የመግዛት አቅምና ፍላጎት ያገናዘበ መሆኑን ከግንዛቤ ማስገባት

3.4. አቅርቦት ትንተና (Supply Analysis )፡-

ፕሮጀክቱ ዒላማ ባደረገው ገበያ የፕሮጀክቱ ምርት የአገር ውስጥና የውጭ አቅርቦት ምን እንደሚመስል ማሳየት

3.5. የፍላጎት-አቅርቦት ክፍተት ትንተና፡- ድርጅቱ ለሚያመርተው ምርት/አገልግሎት በወቅቱ በገበያው ላይ ያለውን የፍላጎትና የአቅርቦት ክፍተት/ልዩነት በማስረጃ በማስደገፍ ትንታኔ ማቅረብ

3.6. ሌሎች፤-

 • ለሚመረተው ምርት/ አገልግሎት የምንጠቀምበትን ግብዓቶች አማራጭ አቅራቢዎች ተገኘነት፣
 • ከአካባቢ ደህንነትና ከጤና አንፃር ክልከላ/ገደብ ስለመኖር/አለመኖሩ፣
 • የሠለጠነ የሰው ሃይል ተገኝነትና የክፍያ መጠን፣
 • ለዋና ዋና ገበያዎች ያለው ቀረቤታ
 • ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ የተመቻቸ ሁኔታ (መሠረተ ልማት) ስለመኖሩ

3.7. የዋጋ ትንተና፡-  በገበያው ያለው የምርቱ/አገልግሎቱ ዋጋ ቢያንስ ያለፉት 5 ዓመታት መረጃና የፕሮጀክቱን ገቢና ወጪ መሰረት በማድረግ ድርጅቱ የምርቱን/አገልግሎቱን ዋጋ እንዴት እንደተመነና በዚህ ዋጋ እንዴት በገበያው ተወዳዳሪ እንደሚሆን ማሳየት

3.8.  ማርኬቲንግ ስትራቴጂ:- ድርጅቱ ምርቱን/አገልግሎቱን ለመሸጥ የሚጠቀምባቸው የሽያጭና ማስተዋወቂያ ዘዴዎችን/ስልቶችን መዘርዘር

3.9.  የጥንካሬ፣ ድክመት፣ ምቹ ሁኔታና ሥጋት ትንተና/SWOT Analysis፤ ድርጅቱ ያለውን ጥንካሬና ድክመት እንዲሁም ከአካባቢው/ውጭ ኃይል የሚገጥሙትን ምቹ ሁኔታዎችና ሥጋቶች ትንታኔ ማቅረብ

 1. የቴክኒክ ጥናት

4.1 የፕሮጀክቱ የመስሪያ ቦታ ሁኔታ፡- የፕሮጀክቱ  መልክዓምድራዊ መገኛ ቦታ በመጥቀስ የመስሪያ ቦታው ከጥሬ ዕቃ አቅርቦት፣ ለማምረት ሂደት፣ ምርትን ለገበያ ከማቅረብ አንፃር አመቺ መሆኑን መግለፅ ያስፈልጋል፡፡

4.2 የፕሮጀክቱ ምህንድስና/Project Engineering;- በዚህ ክፍል የሚከተሉት የፕሮጀክቱ ምህንድስናዊ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ

4.2.1   ግንባታና የሲቪል ሥራዎች፤- የማምረቻ አዳራሽ፣ የጥሬ እቃና የተጠናቀቁ ምርት ማከማቻ መጋዘን፣ ወርክሾፕን ያካተተው የማምረቻ ህንፃው አቀማመጥ  ለምርት ሂደቱ አመቺ መሆኑን በማረጋገጫ ማሳየት

4.2.2    ማሽነሪና ቁሳቁሶች፡- የማሽነሪዎች አቅምና የአጠቃቀም ሆኔታ፣ የማሽንና መሳሪያዎች  ዝርዝር እና የወጪ ክፍልፋይ፣ አስፈላጊ መለዋወጫዎች ዝርዝር፣ የማሽን ተከላ መርሃግብር፣ ለምርት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ተገኝነትና ወጪ ወዘተ… መገለጽ አለበት

4.3 መገልገያ እና የመሠረተ ልማት ተገኝነት፤ ፕሮጀክቱን በተቃና ሁኔታ ለማንቀሳቀስ የሚያስችሉት መገልገያዎች እንደ ውሃ፣ መብራት፣ መንገድ የመሳሰሉት መሠረተ ልማቶች የተሟሉ ስለመሆኑና ወጪያቸውን መግለጽ

4.4 የምርት ሂደት፡- የድርጅቱ ምርት የሚያልፍባቸውን ሂደቶች ዝርዝር፣ የአመራረት ሥርዓት፣ የታቀደ የምርት አቅም፣ የወጪ ክፍልፋይ፣ የማከማቻ አስተዳደር እቅድና የሚጠበቅ ወጪ መጠንን መግለፅ

4.5 የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ:- ፕሮጀክቱ በአካባቢው ላይ የሚኖረው ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ፣ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች እንዲሁም አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ለማረም የሚጠቀማቸውን ዘዴዎች መግለጽ ይኖርበታል፡፡

 1. አደረጃጀት፣ አስተዳደር እና የሰው ሃይል

5.1 የድርጅቱ መዋቅር፡- ድርጅቱ የሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች፣ ያላቸው የሥራ ድርሻና ክፍፍል፣ ትብብርና ቁጥጥር፣ ድርጅታዊ ዓላማ ማሳካት ላይ ያተኮረ መሆኑ

5.2 የድርጅቱ አመራር ሙያ፣ ልምድ እና ክህሎት ዳሰሳ፡- ድርጅቱን የሚመራው ግለሰብ የሥራ ልምድ፣ ብቃትና ያለውና የመምራት አቅም

5.3 የሰው ኃይል፡- ድርጅቱ የሚስፈልገው ክህሎት ያለውና ክህሎት የሌለው ባለሙያ ብዛትና ተገኝነት፣ የምልመላ ሥልጠና እቅድ፣ የሠራተኛ ደመወዝ፣ ማበረታቻና ጥቅማጥቅሞች፣

 1. የፋይናንስ ትንተና (Financial Analysis)፤- የፕሮጀክቱን ግምታዊ የገንዘብ ወጪ፣ የፋይናንስ ሥርዓትና ከፕሮጀክቱ የሚጠበቀውን ገቢ ያካትታል፡፡

6.1. የታቀደ ኢንቨስትመንት፤ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ ለካፒታል ዕቃዎችና ለሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልገው የፋይናንስ መጠን፣ የፋይናንስ ማድረጊያ ዘዴ እና የተበዳሪው መዋጮ ግዴታን ያካትታል

6.2.  አጠቃላይ የሽያጭ/ገቢ መጠን ትንበያ(revenue prediction)፡- ድርጅቱ ባስቀመጠው የጊዜ መርሐ ግብር (time schedule) ምን ያህል ገቢ ለመሰብሰብ እንዳቀደ ያመለክታል

6.3.  የክወና ወጪዎች (Operating Cost)፡- ፕሮጀክቱ ምርት/አገልግሎቱን ለመተግበር የሚስፈልጉ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎችን ለይቶ ማሳየት

6.4.  የተተነበየ የፋይናስ መግለጫ (Projected Financial Statement):- የወጪ እና ገቢ መግለጫ(Income statement):- የትርፍ እና ኪሳራ ትንበያ፣ የገንዘብ ፍሰት ትንበያ፣ የሃብት እና እዳ መግለጫን ያካትታል፡፡

6.5.  የፕሮጀክት ውጤታማነትና ሌሎች የአዋጭነት መለኪያዎች

6.5.1.   የኢንቨስትመንት ተመላሽ/Return on investment፡- በፕሮጀክቱ ኢኮኖሚያዊ እድሜ ከኢንቨስትመንት ወጪው የሚገኝ ገቢ/ተመላሽ በመቶኛ ያሳያል

6.5.2.   የተጣራ ወቅታዊ ዋጋ/Net Present Value:- የፕሮጀክቱ የወደፊት የጥሬ ገንዘብ ፍሰት ወቅታዊ ዋጋ ተመንን የሚያመለክት ነው፡፡

6.5.3.    የትርፍና ኪሳራ ነጥብ ምርት/Brea-Even Point/:- ፕሮጀክቱ በአንድ በተወሰነ የመሸጫ ዋጋ ትርፍም ይሁን ኪሳራ የማያስመዘግብበትን ዝቅተኛ የሽያጭ መጠን ለማስላት ያገለግላል፡፡

6.5.4.   የእዳ መመለሻ ዘመን፡- ፕሮጀክቱ የመጀመሪያውን የኢንቨስትመንት ወጪ ለመመለስ/ ከፍሎ ለመጨረስ የሚያስፈልገውን ጊዜ ያመለክታል

 1. ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታዎች:- ድርጅቱ ለህብረተሰቡ ምን ያህል የስራ ዕድል እንደፈጠረ  ወይም ለመፍጠር እንዳቀደ፣ ለመንግስት የሚከፍለው ዓመታዊ የገቢ ግብር መጠን፣ ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ምን እንደሚመስል፣ የውጭ ምንዛሪን ለማስገኘት ወይም የውጭ ምንዛሪን ለማዳን ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ያለው አስተዋጽኦ በማሳየት የፕሮጅከቱን አስፈላጊነት ማረጋገጥ
 2. መደምደሚያና ምክር ሃሳብ፡- ከላይ ጀምሮ የተዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮችን በአጭሩ በመዳሰስ ማጠቃለልና ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት የሚያግዙ ጉዳዮችን በመጠቆም ጥናቱን መዝጋት::