ከብር 10 ሚሊዮን እና ከዚያ በታች የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት ለሚጠይቁ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች  የንግድ ዕቅድ ይዘት፤

  1. ማጠቃለያ/Executive summary

የንግድ ዕቅዱን አጠቃላይ ይዘት ከአንድ ገፅ ባልበለጠ ቦታ ይዳስሳል፤ ይኸውም የንግድ እቅዱ ጠቀሜታ፣ የምርት ጥራት እና አቅርቦት፣ የገበያ ሁኔታ፣ የገበያ ፉክክር፣ የወጪ እና ገቢ፣ የገንዘብ ፍሰት፣ የሃብት እና እዳ አጠቃላይ የፋይናንስ ትንበያ፣  እና የመሳሰሉት ጉዳዮችን፣ የፕሮጀክቱ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባጭሩ ይዳስሳል፡፡

  1. የፕሮጀክቱ ዳራ/ Project Background

ስለ አመልካቹንና ፕሮጀክቱ አጠቃላይ መረጃዎችን ያብራራል፤

2.1.  የመልካቹ ሥም

ሀ. አመልካቹ የተፈጥሮ ሰው ከሆነ፤ ሥም እስከ አያት ድረስ

ለ. አመልካቹ ህጋዊ ሰውነት ያለው ከሆነ፤ የድርጅቱ የንግድ ሥያሜ

2.2.  አድራሻ

ሀ. የአመልካቹ አድራሻ:- ሥም፣ የመ.ሣ.ቁ፣ ቀበሌ… ወረዳ … የቤት ቁጥር … ስልክ ቁጥር …..

ለ. የፕሮጀክቱ አድራሻ፤ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣  ቀበሌ…  የቤት ቁጥር … ስልክ ቁጥር የመ.ሣ.ቁ፣…..

2.3.  የአመለካቹ የጋብቻ ሁኔታ

2.4.  የፕሮጀክቱ ዓይነት፤ ፕሮጀክቱ የተሰማራበት/የሚሰማራበት ንዑስ የኢኮኖሚ/የሥራ ዘርፍ ማለትም፤ የከብት እርባታ፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ምርት ወዘተ… ይጠቀሳል፡፡

2.5.  የድርጅቱ ዓይነት/ህጋዊ አመሠራረቱ/፡- ድርጅቱ ሲመሰረት የግል ተቋም(solepropritorship)፣ በአጋር (partnership)፣ ኩባንያ(corporation) ፣ ኃላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት(limited liability company) መሆኑ

2.6.  የፕሮጀክቱ ሁኔታ፤ ፕሮጀክቱ አዲስ ወይም ነባር ስለመሆኑ

  1. የገበያ ትንተና፤

3.1. አጠቃላይ ዳሰሳ፤ ምርቱ /አገልግቱ ስለሚቀርብበት ገበያ አጠቃላይ ዳሰሳ በማድረግ ለምርቱ /አገልግቱ አስተማማኝ ገበያ ስለመኖሩና ተፎካካሪዎቹን ማሸነፍ እንደሚችል ማሳየት

3.2. ዒላማ ገበያ/Target Market፤ ፕሮጀክቱ ምርቱን/አገልግሎቱን ሊሸጥበት ስላቀደው ገበያና የሸማቹን ሁኔታ ይተነትናል

3.3. አቅርቦት እና ፍላጎት ዳሰሳ፡- የታቀደውን ምርት/አገልግሎት ለማምረት የሚያስፈልገው ግብዓትና ምርቱ በገበያው ውስጥ ያለው አቅርቦትና ገበያው ለምርቱ ያለው ፍላጎት ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር ማሳየት፣

3.4. ተወዳዳሪዎችና የተወዳዳሪነት ምቹ ሁኔታ/የተፎካካሪነት ብልጫ፤ ፕሮጀክቱ ምርቱን የሚያቀርብበት ገበያ ውስጥ ስለሚገኙ ተወዳዳሪዎች ሁኔታና የፕሮጀክቱ ምርት/አገልግሎት ከተወዳዳሪዎች ልዩና ተመራጭ የሚደረጉትን ምቹ ሁኔታዎች ያብራራል

3.5. የገበያ ስልቶች፡- ምን ያህል እንደሚያመርት፣ ምርቱ የትና እንዴት እንደሚሸጥ፣ በምን ያህል ዋጋ እንደሚሸጥ እና ከተፎካካሪዎች በተሻለ ደንበኞችን እንዴት መሳብ እንደሚቻልና የገበያ ክፍፍሉን ማሳየት

3.6. የዋጋ ትመና፡-  ድርጅቱ የምርቱን/አገልግሎቱን ዋጋ እንዴት እንደተመነና በዚህ ዋጋ እንዴት በገበያው ተወዳዳሪ እንደሚሆን ማሳየት

3.7. የጥንካሬ፣ ድክመት፣ ምቹ ሁኔታና ሥጋት ትንተና/SWOT Analysis፤ ድርጅቱ ያለውን ጥንካሬና ድክመት እንዲሁም ከአካባቢው/ውጭ ኃይል የሚገጥሙትን ምቹ ሁኔታዎችና ሥጋቶች በአጭሩ በሠንጠረዥ መልክ ማቅረብ

 

  1. የቴክኒክ ጥናት

4.1. የፕሮጀክቱ መገኛ ቦታና ሳይት፤ ፕሮጀክቱ ስለሚገኝበት መልክዓምድራዊ መገኛ፣ ለግብዓት አቅርቦትና ለገበያ ያለው ቀረቤታ ይገልጻል

4.2. የፕሮጀክቱ ኢንጂነሪንግ መግለጫ፤

ሀ. የማምረቻ ቦታዉ የሲቪል ሥራዎች መግለጫ፤ የህንፃውን አቀማመጥ፤ የማምረቻ አዳራሽ፣ ማከማቻ መጋዘን፣ ወርክሾፕ ሁኔታ ወዘተ… ለምርት ሂደቱ አመቺ መሆኑን መግለጽ

ለ. ማሽነሪና ቁሳቁስ፤ ለፕሮጀክ አስፈላጊ የሆኑ ማሽኖችና ቁሳቁሶች ዓይነት፣ ወጪና የአቅራቢዎች ዝርዝር፣  የማምረቻ ማሽኖችን ንድፈ ሃሳባዊ አቅም፣ የምርት ሂደት መግለጫ፣ የትግበራ እቅድ (የተከላ፣ የሰው ኃይል ተገኝነት፣ የሥልጠና ሁኔታ)፣ የመለዋወጫ ተገኝነት

4.3. የመገልገያ እና የመሠረተ ልማት ሁኔታ፤ ፕሮጀክቱን በተቃና ሁኔታ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችሉት መገልገያዎች እንደ ውሃ፣ መብራት፣ መንገድ የመሳሰሉት መሠረተ ልማቶች የተሟሉ ስለመሆኑ መግለጽ

4.4. የምርት ሂደት፤  ምርቱ የሚያልፍባቸው ሂደቶች፣ የአመራረት ዘዴ፣ የምርት እቅድ፣ወዘተ… ይዘረዝራል

4.5.  የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ:- ፕሮጀክቱ በአካባቢው ላይ የሚኖረው ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ፣ አዎንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች እንዲሁም አሉታዊ ተፅዖኖዎችን ለማረም የሚጠቀማቸውን ዘዴዎች መግለጽ ይኖርበታል፡፡

4.6. አጠቃላይ የድርጊት መርሃ ግብር ፡- ፕሮጀክቱ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ዋና ዋና ተግባራትን መለየት ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ ተግባር ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅና ለትግበራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በመጠንና በዋጋ መቀመጥ ይገባቸዋል፡፡

5   አደረጃጀት፣ አስተዳደር እና የሰው ሃይል

5.1 የድርጅቱ መዋቅር፡- ድርጅቱ የሚያስተዳድራቸው ሠራተኞች፣ ያላቸው የሥራ ድርሻና ክፍፍል፣ ትብብርና ቁጥጥር፣ ድርጅታዊ ዓላማ ማሳካት ላይ ያተኮረ መሆኑ

5.2 የድርጅቱ አመራር ሙያ፣ ልምድ እና ክህሎት ዳሰሳ፡- ድርጅቱን የሚመራው ግለሰብ የሥራ ልምድ፣ ብቃትና ያለው የመምራት አቅም

5.3 የሰው ኃይል፡- ድርጅቱ የሚስፈልገው ክህሎት ያለውና ክህሎት የሌለው ባለሙያ ብዛትና ተገኝነት፣ የምልመላ ሥልጠና እቅድ፣ የሠራተኛ ደመወዝ፣ ማበረታቻና ጥቅማጥቅሞች፣

6   የፋይናንስ ዕቅድ

የፕሮጀክቱን ግምታዊ የገንዘብ ወጪ፣ የፋይናንስ ሥርዓትና ከፕሮጀክቱ የሚጠበቀውን ገቢ ያካትታል፡፡

6.1 የታቀደ ኢንቨስትመን፤ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ ለካፒታል ዕቃዎችና ለሥራ ማስኬጃ የሚያስፈልገው ፋይናንስ መጠን፣ የፋይናንስ ስልት እና የተበዳሪው መዋጮን ያካትታል

6.2 አጠቃላይ የሽያጭ/ገቢ መጠን ትንበያ(revenue prediction)፡- ድርጅቱ ባስቀመጠው የጊዜ መርሐ ግብር (time schedule) ምን ያህል ገቢ ለመሰብሰብ እንዳቀደ ያመለክታል

6.3 የክወና ወጪዎች (Operating Cost)፡- ፕሮጀክቱ ምርት/አገልግሎቱን ለመተግበር የሚስፈልጉ ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎችን ለይቶ ማሳየት

6.4 የወጪ እና ገቢ ትንበያ(Income statement):- የትርፍ እና ኪሳራ ትንበያ፣ የገንዘብ ፍሰት ትንበያ፣ የሃብት እና እዳ መግለጫን ያካትታል፡፡

7   ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ

ድርጅቱ ለህብረተሰቡ ምን ያህል የስራ ዕድል እንደፈጠረ  ወይም ለመፍጠር እንዳቀደ፣ ለመንግስት የሚከፍለው ዓመታዊ የገቢ ግብር መጠን፣ ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ምን እንደሚመስል፣ የውጭ ምንዛሪን ለማስገኘት ወይም የውጭ ምንዛሬ ለማዳን ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ያለው አስተዋጽኦ

  1. መደምደሚያ እና  አስተያየት፡- አዲስ ድርጅት ለማቋቋምም ሆነ ነባሩን ለማስፋፋት ከላይ የቀረቡ ማሳመኛ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ የማጠቃለያና የመፍትሄ ሃሳብ በማቅረብ ፕሮጀክቱ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት እንደሚያስፈልገው ማሳየት