1. የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ዝርዝ
  2. ማመልከቻ

የባንኩን የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የሚፈልጉ አመልካቾች ጥያቄያቸውን የሊዝ መጠኑንና ሊገለገሉበት ያቀዱትን የካፒታል ዕቃ ዓይነት በመጥቀስ በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ፈቃድ

2.1 የንግድ ሥራ  ፈቃድ

2.2 የዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት

2.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር

  1. መሬት/ የማምረቻ ቦታ/

Ø  የማምረቻ ቦታው የተሟላ መገልገያ ( መብራት፣ ውሀ) ስለመኖሩ  ማረጋገጫ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

Ø  በተጨማሪም ቦታው ለምርት አመቺና ተገቢ መሆን ይኖርበታል፡፡

3.1 የግል ይዞታ ከሆነ፤

  • በሚመለከተው የመንግስት አካል የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ኮፒ

3.2 ከመንግስት በኪራይ የተገኘ ከሆነ፤

  • የማምረቻ ቦታው የኪራይ ዘመን ከካፒታል ዕቃው የኪራይ ዘመን ጋር የተጣጣመና በሚመለከተው አካል የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል፣
  • አከራዩ የመንግስት አካል ተከራዩ የማምረቻ ማሽኑን በቦታው መትከል እንደሚችል መፍቀድና መስማማት ይገባዋል፡፡ ይህም በኪራይ ውሉ መካተት ይኖርበታል፡፡
  • ተከራዩ ግዴታውን ባለመወጣቱ የማምረቻ ቦታው ለሶስተኛ ወገን መተላለፍ የሚችል መሆን አለበት፡፡ ይህም በኪራይ ውሉ መካተት ይኖርበታል፡፡

3.3 ከግለሰብ በኪራይ የተገኘ ከሆነ፤

  • የኪራይ ውሉ በሚመለከተው አካል የተመዘገበ መሆን ይኖርበታል፣
  • የማምረቻ ቦታ የኪራይ ዘመን ቢያንስ የአንድ ዓመት ሆኖ እስከ ካፒታል ዕቃው የኪራይ ዘመን መጨረሻ ድረስ በየአመቱ የሚታደስ መሆን አለበት፡፡
  • ፕሮጀክቱ የማምረቻ ማሽን በቦታው በቋሚነት እንዲተከል የሚያስገድድ ከሆነ የማምረቻ ቦታው የኪራይ ዘመን ቢያንስ ከማምረቻ ዕቃው የኪራይ ዘመን ጋር የተጣጣመ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • አከራዩ ለተከራዩ የማምረቻ ማሽኑን በቦታው መትከል እንደሚችል መፍቀድና መስማማት ይገባዋል፡፡ ይህም በኪራይ ውሉ መካተት ይኖርበታል፡፡
  • አከራዩ የኪራይ ውሉን ማፍረስ ካሰበ ለተከራዩ ቢያንስ ሦስት ወራት አስቀድሞ በጽሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህም በኪራይ ውሉ መካተት ይኖርበታል፡፡
  • የማሽነሪ የማምረቻ ቦታ ማዘዋወር ከተከሰተ ወጪው በተከራዩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  1. ዋጋ ማሳወቂያ ደረሰኝ / Pro-forma invoice/

አመልካቹ የዋጋ ማሳወቂያ ደረሰኝ ከተለያዩና ቢቻል ከሦስት አምራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ካላቸው አቅራቢዎች ማቅረብ ይገባዋል፡፡

የሚቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ደረሰኝ የሚከተሉትን ማካተት ይኖርበታል፡-

  • የሻጩን ስምና አድራሻ
  • የገዢውን ስምና አድራሻ
  • የሽያጭ ሁኔታ
  • የክፍያ ሁኔታ
  • የተመረተበት ሀገር
  • ዕቃውን የሚያስረክቡበት ቀን
  • ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫዎች (technical specification )
  1. ውክልና ( ስልጣን )

በሦስተኛ ወገን የሚቀርብ የሊዝ ፋይናንስ ጥያቄ/ማመልከቻ፤ አግባብ ካለው አካል የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ ባላቸው ወኪሎች መቅረብ ይኖርበታል፣

  1. የቅድመ ሥራ ታሪክ መዝገብ ( track record )

አመልካቹ ከዚህ ቀደም የሚያንቀሳቀሰው ድርጅት ካለው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ከዚህ እንደሚከተለው ማቅረብ አለበት

ተ.ቁ

የአመልካች ስም

የድርጅቱ አድራሻ

ድርጅቱ ያለበት ሁኔታ/የሥራ ደረጃ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

6.1. የሂሳብ መግለጫ

ከሦስት ዓመት ያልበለጠ ጊዜያዊ/ያልተረጋገጠ የሂሳብ መግለጫ (provisional financial statements) ወይም በተፈቀደላቸው የሂሳብ መርማሪዎች የታየ (የተጣራ) የሂሳብ መግለጫዎች (audited financial statements) ማቅረብ አለበት፡፡

6.2. የአመልካቹ / የባለቤቱ /  የብድር ታሪክ

የሚከተሉትን ጉዳዮች ያካተተ የብድር ታሪክ  ማስረጃ/ማረጋገጫ ከአበዳሪው ባንክ ወይም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም መቅረብ ይኖርበታል፤

  • የአበዳሪው የገንዘብ ተቋም ሥም
  • የተበደረበት ቀን
  • ስንት ጊዜ እንደተበደረ
  • ብድሩ የሚጠናቀቅበት ጊዜ
  • የብድር አመላለስ ሁኔታ
  • የተበዳሪው የዕዳ ሁኔታ

7         የግብር ግዴታ በአግባቡ ስለመወጣቱ ከሚመለከተው አካል የማረጋገጫ ደብዳቤ

8         የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ እንደ ፕሮጀክቱ ዓይነት ከሚመለከተው አካል የማረጋገጫ ደብዳቤ

9         የአመልካቹ ማህበራዊ መስተጋብር

አመልካቹ በማኅበረሰቡ ዘንድ በጥሩ ሰብዕናው የሚታወቅ እና ሰርቶ የመለወጥ አመለካከት ያለው ስለመሆኑ ከማህበራዊ ተቋማት እንደአስፈላጊነቱ ማረጋገጫ ደብዳቤ

10      አስተዳደር፡- አመልካቹ የሚከተሉትን መረጃዎች ያካተተ የድርጅቱን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይም የፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የማስተዳደር አቅም የሚያመለክቱ ማስረጃዎች (CV) ከማጣቀሻ ሠነዶች ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፤

  • አድራሻ
  • የትምህርት ታሪክ
  • የስራ ልምድ

11      የድርጅቱ / የግለሰቡ  መዋጮ ምንጭ (Source of equity) አመልካቹ የሚጠበቅበትን መዋጮ ለማቅረብ የሚጠቀመውን ገንዘብ ምንጭ በግልጽ ማሳየት ይኖርበታል፡፡

12      የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ፡-

በመንግስት የተደራጁና ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ/ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከሚመለከተው የመንግስት አካል የሚከተሉትን ማስረጃዎች እንደአስፈላጊነቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12.1     በባንኩ የሚሰጠውን የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ የድጋፍ ደብዳቤ፣

12.2     ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሥልጠናዎችን (የኢንተርፕረነርሺፕ፣ ገበያ፣ ሂሳብ አያያዝ፣ ቴክኒክ፣ ወዘተ…) ስለማግኘታቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ

13      የንግድ ዕቅድ ወይም የአዋጭነት ጥናት/ ዝርዝር ሁኔታው ከዚህ ጋር በተያያዘው ቅጽ መሠረት/

  1. ነባር ፕሮጀክቶችን ለማስፋፋት የሚያስፈልጉ መረጃዎች
  2. በአንቀጽ I ከ ተ.ቁ 13 ውጭ ከተራ ቁጥር 1-12 የተዘረዘሩት ሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች 
  3. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ
  4. የማስፋፊያ ፈቃድ (እንደአስፈላጊነቱ)
  5. ተጨማሪ ካፒታል ፤ የተመዘገበው ካፒታል በቂ ካልሆነ
  6. የተመረመረ የሂሳብ መግለጫ ቢያንስ ያለፉት ሦስት ዓመታት
  7. የአካባቢ ደህንነት ግዴታውን በአግባቡ ስለመወጣቱ ከሚመለከተው አካል የማረጋገጫ ደብዳቤ
  8. ለሚስፋፋው ፕሮጀክት ዝርዝር የንግድ ዕቅድ
  9. የግብር ግዴታ ስለማሟላቱ የማረጋገጫ ደብዳቤ
  10. የነባር ሠራተኞች የሥራ ልምድ ማስረጃ እና ፔይሮል ዝርዝር
  11. የጥሬ ዕቃ ዝርዝር፤ የተገዛበትን ዋጋና ቀን ጨምሮ
  12. የነባር ቋሚ ንብረቶች ዝርዝር፤ የተገዛበትን ዋጋና ቀን ጨምሮ
  13. ቢያንስ የአንድ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት

ተ.ቁ

የምርት ዓይነት

ዓመት 1

ዓመት 2

ዓመት 3

ብዛት

ዋጋ

ብዛት

ዋጋ

ብዛት

ዋጋ

1

ምርት 1

 

 

 

 

 

 

2

ምርት 2

 

 

 

 

 

 

3

ምርት 3

 

 

 

 

 

 

4

ሽያጭ

 

 

 

 

 

 

4.1 ሀገር ውስጥ

 

 

 

 

 

 

4.2 ኤክስፖርት

 

 

 

 

 

 

  1. ሁሉም ማስረጃዎች የፕሮጀክቱን እውነተኛ የፋይናንስ ሁኔታ የሚያሳይ መሆኑን የሚገልፅና የተፈረመ መግለጫ መቅረብ ይኖርበታል፡፡