የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

በኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር አስተባባሪነት ለሃገር መከላከያ ሰራዊት እና በጦርነቱ ለተጎዱ አካላት ድጋፍ የሚውል ገንዘብ ለማሰባሰብ የአዲስ አበባከ ተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባደረጉት ጥሪ መሰረት ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው መርኃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ፒ.ኤች.ዲ) በሁነቱ ላይ በአካል ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

በመርኃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የባንኮች ማኅበር ፕሬዚዳንት እና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ጀነራሎች የተገኙ ሲሆን ባንኮቹ ለቀረበው ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠታቸው ድጋፍ በተደረገላቸው ወገኖች ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡