ባንኩ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ውይይት አደረገ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር በትብብር መሥራት በሚችልባቸው አስቻይ ሁኔታዎች ዙሪያ ጥር 26 ቀን 2014 .ም በባንኩ ዋናው መሥሪያ ቤት ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ ላይ የባንኩ ፕሬዚዳንት የተከበሩ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው /.ኤች./ እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ከማዕድን ሚኒስቴር በኩል ደግሞ የተከበሩ አቶ ታከለ ኡማ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት የተከበሩ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው (.ኤች.) ስለባንኩ ፖሊሲዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ብድር ስለሚሰጥባቸው መስፈርቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከብድር ሥራ ጎን ለጎን በስልጠና እና በትብብር /partnership/ መሥራት ስለሚቻልባቸው አስቻይ ሁኔታዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው በቀጣይ በማዕድን ልማት ዘርፍ ከባንኩ ጋር በትብብር በመሥራት በአገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡