በባንኩ ፣ የጀርመኑ KFW እና ግብርና ሚኒስቴር መካከል የፊርማ ሥምምነት ተደረገ

 

 ጀርመን የ15 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል

በኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የጀርመኑ ኬ.ኤፍ. ደብሊው (KFW) እና ግብርና ሚኒስቴር መካከል በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የግብርና ሜካናይዜሽን ማሽነሪ ለአርሶ አደሮች በኪራይ ለማቅረብ የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ ፊርማ ሥነ ሥርዓት ህዳር 01 ቀን 2012 ዓ.ም በጀርመን ልማት ትብብር ጽ/ቤት (German Development Cooperation Office)ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ፣ የጀርመኑ KFW የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ክላውስ ሙለር እና የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሳኒ ረዲ ፈርመዋል፡፡

የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ የግብርና ምርትንና ምርታማነትን ለመጨመርና የሜካናይዜሽን እርሻን ለማበረታታት እንደደሆነ ተገልጿል፡፡

የጀርመን መንግስት የአርሶ አደሮችን የግብርና ምርት ለማሳደግ የሚረዳ የ15 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ድጋፉ የባንኩን የማበደር አቅም የሚያሳድግ መሆኑንና በስምምነቱ መሠረት ባንኩ ብድሩን ለተጠቃሚዎች ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡