የቋሚ ኮሚቴ አባላት ከባንኩ ጋር ውይይት አካሄዱ፤ ጉብኝት አደረጉ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ5ወር የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ከከፍተኛ ሥራ መሪዎች ጋር ግምገማዊ ውይይት ታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. አካሂደዋል፤ የመስክ ጉብኝትም አድርገዋል፡፡

 

 

ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ስለባንኩ የውስጥ አሠራር፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር፣ የሪፎርምና መልካም አስተዳደር ሁኔታ፣ የፕሮጀክት አስተዳደር እና ከዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ገለጻ ተደርጓል፡፡

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ባንኩ ትርፍ ማስመዝገቡም ተብራርቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለእርሻ ሥራ ተበድረው ስላልሰሩ ባለሃብቶች፣ ስለተበላሽ ብድር፣ ህዝቡ ስለ ባንኩ ያለውን አመለካከት ለመቀየር የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈላጊነት እና በመሳሰሉት ዙሪያ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

በምላሹም ለእርሻ ሥራ ብድር ወስደው ባልመለሱ ሃለሃብቶች እና የተበላሸ ብድርን በሚመለከት እጃቸው ያለበት ሰዎች ለህግ እየቀረቡ እንደሆነ፣ በባንኩ የተገዙ ኢንቨስትመንቶች እየተሰበሰቡ እንደሚገኝ፣ ለገጽታ ግንባታ ሥራ በአምስት ዓመቱ የባንኩ ስትራቴጂክ ሪፎርም እቅድ ውስጥ መካተቱ ተብራርቷል፡፡

በመቀጠል የቋሚ ኮሚቴው አባላት የባንኩ ፕሮጀክቶች በሆኑት አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ እና ቢ.ኤም.ቲ. ኬብል ማምረቻ ፋብሪካዎች ጉብኝት አካሂደዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረበው ገለጻ እና በመስክ ጉብኝቱ አባላቱ ስለ ባንኩ የነበራቸው ግምት መቀየሩን እና የተሻለ ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡