የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰጠው ብድር ማካካሻ የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተመለከቱትን የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች እና መካናይዝድ እርሻ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 98/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የተበዳሪው /የመያዣ ሰጪው/ ስም |
የሚሸጠው ንብረት(ኘሮጀክት) አድራሻና አይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የጨረታ ሁኔታ |
የጨረታው ደረጃ |
የጨረታው ቀንና ሰዓት |
አይካ አዲስ ቴክስታይልና ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የገል ማህበር |
በሰበታ ከተማ አስተዳደር አለም ገና ወረዳ ቀበሌ 08 በ205,000 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ የተቋቋመ የተቀናጀ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከነሙሉ ግንባታዎች፤ተሽከርካሪዎችን የምርት መሳሪያዎች፤ልዩ ልዩ መለዋወጫዎች ጥሬ ዕቃና ሙሉ በሙሉ ያለቀለት ምርት፤
|
1,956,601,072..76 |
ዝግ ጨረታ |
ሁለተኛ |
ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00ሰዓት |
ኤልሲ አዲስ ኢንደስትሪያል ዲቨሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
በአዳማ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 05 ክልል ውስጥ በ149,651 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ የተቋቋመ የጨርቃ ጨርቅና የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ ከነሙሉ ግንባታዎች፤ የምርት መሳሪያዎች፤ ዕቃዎች እና ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ |
886,244,136.86 |
ዝግ ጨረታ |
ሁለተኛ |
ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00ሰዓት |
ኤንጅልስ ከተን ኤንድ ቴክስታይል ፕሮደክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን፣ ለገጣፎ ለገዲዳ ከተማ ቀበሌ 02 ውስጥ በ25ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተቋቋመ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ከነሙሉ ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ተሸከርካሪዎችና ሌሎች ተያያዥ ንብረቶችን ጨምሮ |
258,819,423.22 |
ልዩ ድርድር |
- |
ጥር 5 ቀን 2012 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00-10፡00ሰዓት |
ኦሞ ቫሊ ፋርም ኮኦፐሬሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
በደቡብ ኦሞ ዞን፤ሐመር ወረዳ፤ ካራ ቆሪቾ ቀበሌ ውስጥ በ10,000 ሄክታር መሬት ላይ የተቋቋመ የጥጥ እርሻ ልማት ከነሙሉ ግንባታዎች፤ የምርት መሳሪያዎች፤ ዕቃዎች እና ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ |
166,555,569.36 |
ልዩ ድርድር |
- |
ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከ8፡00-10፡00ሰዓት |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቱን የሚገዙበትን ንብረት አይነት፤ የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸዉን በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በሰም በታሸገ ኢንቬሎኘ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከሶስተኛዉ ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናዉ መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን እስከ ጥር 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ይካሄዳል፤
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
- አይካ አዲስ ቴክስታይልና ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኃ/የተ/የገል ማህበር፣ኤልሲ አዲስ ኢንደስትሪያል ዲቨሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ኤንጅልስ ከተን ኤንድ ቴክስታይል ፕሮደክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የምርት ስራቸው ያልተቋረጠ በመሆኑ አሸናፊው ከግዢው ዋጋ በተጨማሪ በመጓጓዝ ወይም በክምችት ላይ ያሉ ግብአቶች /ጥሬ ዕቃዎች/ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ያለቁ ምርቶችን በርክክብ ወቅት በሚደረስበት የትመና ዋጋ መሰረት በጥሬ ገንዘብ /በዱቤ/ ከፍሎ መውሰድ አለበት፤
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና ፕሮጀክቱን የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
- በጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው፤
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት II በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011--524-53-73 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ ንብረቱን መጐብኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
ቦርዱ ከሠራተኞች ጋር ስብሰባ አካሄደ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቦርድ ሥራ አመራር ከባንኩ ሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ጋር ጥቅምት 26 ቀን 2ዐ12 ዓ.ም በኦሮሞ ባህል ማዕከል ስብሰባ አካሂዷል፡፡
የስብሰባው ዋና ዓላማ ከቦርዱ ጋር ትውውቅ ማድረግና ቦርዱ ያዘጋጀውን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ማቅረብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቦርድ ሥራ አመራር ሰብሳቢ ዶ/ር ተገኘወርቅ ጌጡ በስብሰባው መክፈቻ ላይ ባንኩ ከ11ዐ ዓመት በላይ በሆነው ዕድሜው ለአገራችን ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ገልጸው፤ እንደቻይና፣ ብራዚል፣ ህንድ እና ፈረንሳይ አሁን ለደረሱበት የኢኮኖሚ ማማ መሠረታቸው የልማት ባንኮቻቸው መሆናቸውንም አክለዋል፡፡
ሆኖም ልማት ባንክ እንደሌሎች ዓለም አቀፍ ባንኮች ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲቀጥል ለማስቻል ቦርዱ የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ማዘጋጀቱን፤ በዕቅዱ የባንኩን ታሪካዊ ዳራ፣ አሁን ያለበት አቋም እና በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ የት መድረስ እንዳለበት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመቀጠል በባንኩ የቦርድ አባልና የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የ5 ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ (እ.ኤ.አ. ከ2019-2023) አቅርበዋል፡፡
በስትራቴጂክ እቅዱ ባንኩ ከሌሎች ንግድ ባንኮች የተለየ ስለመሆኑ፤ ከዚህ ቀደም የነበረው ቢዝነስ ሞዴል ከአሠራር፣ ገቨርናንስ እና መዋቅር አኳያ ክፍተቶች የነበሩበት በመሆኑ አዲስ የቢዝነስ ሞዴል እንደሚያስፈልገው ተብራርቶ ቀርቧል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የባንኩን 27% የብድር ድርሻ የያዙትን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ የቦርድ አባልና የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ በበኩላቸው ቦርዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ባንኩን በጥልቀት አጥንቶ ወደ ሥራ መግባቱን አድንቀዋል፡፡ ባለፈው በጀት ዓመት በብድር አሰባሰብ እና ክትትል ሥራ ላይ የነበሩ የሥራ ርብርብ ጥሩ እንደነበርም አክለዋል፡፡ ሆኖም ለብድር የተያዘ የመጠባበቂያ ወጪ /Provision/ አያያዝ ስርዓታችን መፈተሽ እንዳለበት እና በዓለም አቀፉ የሒሳብ ሪፖርት ሥርዓት /IFRS/ መሠረትም የምንሰራበት ይሆናል ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ ቦርዱ ከያዘው ስትራቴጂክ ዕቅድና የለውጥ /ሪፎርም/ ሥራ ጋር በመሆን ባንኩ አሁን ካለበት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ በማድረግ እናሻግረዋለን ብለዋል፡፡
በመቀጠል የቦርድ ሰብሳቢው መድረኩን ለተሰብሳቢዎች ክፍት አድርገው የተለያዩ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ተቀብለዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል ቦርዱ ያዘጋጀው የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ጥሩ እንደሆነና የባንኩ ሠራተኞች እቅዱን ከግብ ለማድረስ ተግተው እንደሚሰሩ፣ ባንኩን በአግባቡ ሊጠቅሙ የሚችሉ ሆኖም ትኩረት ያልተደረገባቸው የሥራ ክፍሎች ስለመኖራቸው፣ ከኑሮ ውድነቱ አንጸር የደመወዝማ ሻሻያ፣ የቦነስ እና እርከን ጭማሪ ጉዳይ፣ የባንኩን ገጽታ ለመገንባት ለሚዲያ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት ስለማስፈለጉ፣ ከምደባ፣ ዝውውርና እድገት አኳያ ክፍተቶች እንዳሉ፣ የባንኩ ችግሮች አብዛኛው ምንጭ ከውጭ አካላት ስለመሆኑና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በመጨረሻም የቦርድ ሰብሳቢው የተነሱት ሀሳቦችና ጥያቄዎች ጥሩ እንደሆኑ እና በ5 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅዱ ውስጥ በዝርዝር እንደተቀመጡ፤ በሁሉም አቅጣጫ ባንኩን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ፣ ባንኩ ውጤታማ ከሆነ የሠራተኛ ጥያቄዎችን ማለትም ደመወዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ከመመለስ ባሻገር በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ሚና ማሳረፍ እንደሚቻል፤ ስለሆነም ሁሉም የባንኩ ሥራ አመራርና ሠራተኛ ተባብሮ በመሥራት ስትራቴጂክ እቅዱን ከግብ ማድረስ እንደሚጠበቅበት አቅጣጫ ሰጥተው ስብሰባውን ቋጭተዋል፡፡
በባንኩ ፣ የጀርመኑ KFW እና ግብርና ሚኒስቴር መካከል የፊርማ ሥምምነት ተደረገ
ጀርመን የ15 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ የጀርመኑ ኬ.ኤፍ. ደብሊው (KFW) እና ግብርና ሚኒስቴር መካከል በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የግብርና ሜካናይዜሽን ማሽነሪ ለአርሶ አደሮች በኪራይ ለማቅረብ የሚያስችል የፋይናንስ ድጋፍ ፊርማ ሥነ ሥርዓት ህዳር 01 ቀን 2012 ዓ.ም በጀርመን ልማት ትብብር ጽ/ቤት (German Development Cooperation Office)ተፈረመ፡፡
ስምምነቱን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ፣ የጀርመኑ KFW የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ክላውስ ሙለር እና የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሳኒ ረዲ ፈርመዋል፡፡
የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ የግብርና ምርትንና ምርታማነትን ለመጨመርና የሜካናይዜሽን እርሻን ለማበረታታት እንደደሆነ ተገልጿል፡፡
የጀርመን መንግስት የአርሶ አደሮችን የግብርና ምርት ለማሳደግ የሚረዳ የ15 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ድጋፉ የባንኩን የማበደር አቅም የሚያሳድግ መሆኑንና በስምምነቱ መሠረት ባንኩ ብድሩን ለተጠቃሚዎች ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን ለጋዜጠኞች ገልጸዋል፡፡
DBE Undertakes 1st Q Management Meeting
Development Bank of Ethiopia (DBE) had undertaken it’s 2019/20 First Quarter Management Members Meeting on November 01& 02/2019 at the Ministry of Trade & Industry Conference Hall.
At the opening of the meeting, President of the Bank, Ato Haileyesus Bekele said the objective of this meeting is to review and evaluate task performances, identify major problems and discuss on the way forwards.
During the meeting, the 2019/20First Quarter Performance Report of the Bank was presented by Vice Presidents, Strategy, Change and Communication Directorate at the corporate level as well as by three selected districts and profoundly evaluated and discussed over by management members of the Bank.
The report revealed performance of the Bank, problems encountered during the quarter, corrective measures employed, strengths and weaknesses observed, evaluation and monitoring processes and overall the Bank’s loan provision performances were evaluated.
Accordingly, the Bank’s first quarter performance registers satisfactory labeling 85% by approving birr 2.18 billion, disbursing birr 1.98 billion and collecting birr 3.3 billion from project and lease financing services.
The Bank also sold Great Renaissance Dam Bond to birr 167.45 million during the quarter under review.
After the presentation, issues with respect to prudent lending, maximizing collection of loans and reducing NPLs, increasing great renaissance dam bond sale especially in districts, transparent system for promotion and transfer of employees and over all attitudinal change across employees and management members are openly discussed.
Finally, President of the Bank, Ato Haileyesus Bekele urges all management members of the Bank working in different levels should work aggressively to contribute share by scaling up the country’s economy by earning export proceeds and getting tax revenue for the government, creating employment opportunities through projects, increasing collection of loans and reducing NPL ratios in view of credit policies and procedures of the Bank.
Page 27 of 31