ባንኩ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ውይይት አደረገ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር በትብብር መሥራት በሚችልባቸው አስቻይ ሁኔታዎች ዙሪያ ጥር 26 ቀን 2014 ዓ.ም በባንኩ ዋናው መሥሪያ ቤት ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ የባንኩ ፕሬዚዳንት የተከበሩ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው /ፒ.ኤች.ዲ/ እና ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ከማዕድን ሚኒስቴር በኩል ደግሞ የተከበሩ አቶ ታከለ ኡማ እና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት የተከበሩ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው (ፒ.ኤች.ዲ) ስለባንኩ ፖሊሲዎችና አሰራሮች፣ እንዲሁም ብድር ስለሚሰጥባቸው መስፈርቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከብድር ሥራ ጎን ለጎን በስልጠና እና በትብብር /partnership/ መሥራት ስለሚቻልባቸው አስቻይ ሁኔታዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ በተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው በቀጣይ በማዕድን ልማት ዘርፍ ከባንኩ ጋር በትብብር በመሥራት በአገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
ባንኩ ከዲያስፖራ ማኅበረሰብ ጋር ውይይት አካሄደ
ባንኩ የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥሪን ተከትለው ወደ ሀገራቸው ከገቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን /ዲያስፖራ ማኅበረሰብ/ ጋር ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የባንኩ ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የዲያስፖራ ማኅበረሰብ ማህበር ተወካዮች፣ የማህበሩ አባል የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን /የዲያስፖራ ማኅበረሰብ/ ተገኝተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው /ፒ.ኤች.ዲ/ ስለባንኩ የቀድሞ አሠራር፣ አሁንናዊ ሁኔታ እና ለወደፊቱ ሊሰሩ ስለታቀዱ ሥራዎች፣ እንዲሁም የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን መሠረት በማድረግ ስለተጀመሩ የለውጥ ሂደቶች አጠር ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ተረክቦ ማስቀጠል ለሚችል ዳያስፖራ አስፈላጊውን ሂደት ተከትሎ መሥራት የሚችልበት ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በመቀጠል ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ከባንኩ ስለሚፈልጉት እገዛ እና ተያያዥ ጉዳዮች ያሏቸውን ጥያቄዎች እንዲያነሱ መድረኩን ክፍት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን ያነሱ ሲሆን በዋናነትም የባንኩ የብድር አሰጣጥ ሂደትን ቀልጣፋ አለመሆን፣ የውጭ ምንዛሪ አሰጣጥ፣ የወለድ ምጣኔ እና የብድር አመላለስ፣ እንዲሁም የእፎይታ ጊዜን በተመለከተ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው የጠየቁ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ከባንኩ ፕሬዝዳንት በተሰጠው ምላሽ የባንኩ ወለድ ምጣኔ 11.5 መሆኑን ገልጸው ይህም በሃገራችን ካሉ የንግድ ባንኮች አንፃር ሲታይ አነስተኛ መሆኑ ለዳያስፖራው ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ የእፎይታ ጊዜን በተመለከተም እንደፕሮጀክቱ ዓይነት የሚታይ ሆኖ ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት እንደሚሆን ምላሽ ተሰጥቶበታል፡፡
ተሳታፊዎቹ ባንኩ ይህን መድረክ በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ባንኩን ባላቸው የእውቀት እና ቴክኖሎጂ ሙያ ዘርፎች የበኩላቸውን እገዛ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በጉለሌ ክ/ከ በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እና ወረዳ 8 በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ እንደ አዲስ ፈርሰው የተገነቡ 3 የአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለነዋሪዎቹ ተላልፈዋል፡፡
በተዘጋጀው የቤት ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የባንኩ ፕሬዚዳትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ ሌሎች የክፍለ ከተማውና ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
Read more: በጉለሌ ክ/ከ በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ
በባንኩ የገንዘብ ድጋፍ የተገነቡ የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች ተመረቁ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ፈርሰው እንደ አዲስ የተገነቡ 5 የአረጋዊያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤቶች፣ 4 መጸዳጃ ቤቶች እና 1 ምግብ ማብሰያ ቤት ጥር 14 ቀን 2014 ዓ.ም ተመርቀው የቁልፍ ርክክብ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ ፕሬዚዳትና ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና የወረዳ 5 ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት ተገኝተዋል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ፒ.ኤች.ዲ) በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ይህ ተግባር ባንኩ በማኅበራዊ ኃላፊነት ከሚያደርጋቸው መጠነ ሰፊ ድጋፎች መካከል አንዱ ሲሆን ባንኩ ከተቋቋመበት 1901 ዓ.ም ጀምሮ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በልዩ ልዩ መንገዶች ሲወጣ የኖረ የሀገር ሀብትና ኩራት የሆነ አንጋፋ ባንክ ነው ብለዋል፡፡
Page 11 of 30